በደቡባዊ ፖላንድ ሰዎች ታጉረው ይሰቃዩበት የነበረ ካምፕ የተዘጋበት 75ኛ ዓመት እየታሰበ ነው
ናዚ ተቆጣጥሮት በነበረው የፖላንድ ግዛት ኦሾይትዝ በሚባለው ካምፕ ታጉረው ይሰቃዩ የነበሩ ዜጎች ነፃ የወጡበት 75ኛ አመት በእየሩሳሌም ትናንት ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም ታስቦ ውሏል፡፡
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት በናዚ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተለይም አይሁዶች በካምፑ ተጨፍጭፈዋል፡፡
በወቅቱ የሶቪየት ሀይሎች በወሰዱት የተቀናጀ ጥቃት በካምፑ የነበሩትን ነፃ በማውጣት ካምፑን አስዘግተዋል፡፡ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ሆሎካስት የተሰኘ ፎረም በእየሩሳሌም እየተካሄደ ነው፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን፣የአሜሪካው ም/ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስን ጨምሮ ከ40 በላይ የተለያዩ የአለም ሀገራት አመራሮች በፎረሙ ላይ ታድመዋል፡፡
ዘረኝነት አሁንም የዓለም ስጋት እንደሆነና መንግስታት ሊዋጉት እንደሚገባም በፎረሙ ተነስቷል፡፡
ሆሎካስት ከ1941-1945 ድረስ 6 ሚሊዮን የሚጠጉ የአውሮፓ አይሁዶች የተጨፈጨፉበት የዘር እልቂት መጠሪያ ሲሆን የኦሾይትዝ ካምፕ ደግሞ አንዱ የድርጊቱ መፈፀሚያ ስፍራ ነበር፡፡
በዚሁ የተሰየመው የዓለም ሆሎካስት ፎረምም ለ5ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን በእስራኤል ታሪክ ትልቁ የዲፕሎማሲ መድረክ ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ