ትራምፕ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ. ኬነዲ ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይፋ አደረጉ
በብሔራዊ ቤተመዘክር ድረገጽ የወጡት የመጀመሪያዎቹ የኤሌክትሪክ ቅጅዎችና ሌሎች 80ሺ ኮፒዎች በፍትህ ዲፓርትመንት የህግ ባለሙያዎች ከተገመገሙ በኋሃ ይታተማሉ ተብሏል

ፕሬዝደንት ትራምፕ የጥቁር መብት ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄአር. ግድያ የተመለከቱ ሰነዶችንም ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል
ትራምፕ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ. ኬነዲ ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይፋ አደረጉ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከ1963ቱ የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ.ኬኔዲ(ጄኤፍኬ) ግድያ ጋር የተያያዙ ሰነጆች በትናንትናው እለት በመልቀቅ በታሪክ በተፈጸመው አስደንጋጭ ክስተት ላይ ግልጽነት እንዲኖር በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚፈልጉ አሳይተዋል።
በብሔራዊ ቤተመዘክር ድረገጽ የወጡት የመጀመሪያዎቹ የኤሌክትሪክ ቅጅዎችና ሌሎች 80ሺ ኮፒዎች በፍትህ ዲፓርትመንት የህግ ባለሙያዎች ከተገመገሙ በኋሃ ይታተማሉ ተብሏል።
ሚስጥራዊ ሰነዶችን ጭምር የያዙት ዲጂታል ሰነዶች ወደ ኑክሌር ጦርነት ሊያመራ ጫፍ ደርሶ ከነበረው የኩባ የሚሳይል ቀውስ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በአሜሪካና በያኔዋ ሶቭየት ህብረት በአሁኗ ሩሲያ ግንኙነት ዙሪያ ፍርሃት ነግሶ እንደነበር ያሳያሉ።
አብዛኞቹ ሰነዶች የሚያወሱት ገዳዩ ሀርቬይ ኦስዋልድ በሶቭየት ያሳለፈውን ጊዜና በ1963 በዳላስ ኬኔዲ እስከተገደሉበት ድረስ ባሉ ወራት ያደረገውን እንቅስቃሴ ለማወቅ ያደረጉትን ምርመራ ነው። በሰነዱ ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ምርመራ በብዙዎች ዘንድ ይሆናል ተብሎ ከሚታመነው ያፈነገጠ አይደለም።
የትራምፕ የጤና እና የሰው አገልግሎት ጸኃፊ ሮበርት ኤፍ.ኬኔዲ ጄአር. በአጎቱ ግድያ ላይ የአሜሪካ ሴንትራል ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ(ሲአይኤ) እጁ አለበት ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
የጄኤፍኬ የልጅ ልጅ የሆነችው ጃክ ስችሎስበርግ በኤክስ ገጹ የትራምፕ አስተዳደር መረጃውን ሊለቅ መሆኑን ለማንኛውም የኬኔዳ ቤተሰብ አላወቀውም ብሏል። በጄኤፍ ኬ ላይ መጽሀፍ የጻፉት የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ፍሬድሪክ ሎግቫል የሰነዶቹ መለቀቅ የጎደሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሊረዳ እንደሚችል ገልጸዋል።
"ምንም ሳይቀናነሱ ሙሉ ሰነዶችን ማግኘት አስፈላጊ ነው። ነገርግን ስለግድያው ከዚህ በፊት ያወቅነውን የሚያስቀይር የተለየ ውጤት ይገኛል ብዬ አላስብም"
አንድ ሚስጥር የሚል ሰነድ የተጻፈበት ሰነድ የዋረን ኮሚሽን ሲአይኤና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሶቭየትዋ ሴትና ግድያ ፈጽሟል በተባለው አሜሪካዊ ኦስዋልድ መካከል ስላለው የጋብቻ ግንኙነት የሰጡት መረጃ ስላለው ልዩነት የሲአይኤ ሰራተኛን ሊ ዊግሬን ጠይቆ በእጅ ጽሁፍ ያሰፈረበት ነው። በርካታ አሜሪካውያን ጄኤፍኬ በሴራ ተገድለዋል ብለው ያምናሉ።
ትራምፕ ባለፈው ጥር ወደ ኃይትሀውስ ከገቡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ሰነዶቹ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ያስተላለፉት። ይህን ተከትሎ የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ከዳላሱ የኬኔዲ ግድያ ጋር የተያያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰነጆች ለመፈለግ ተገደዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ የጥቁር መብት ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄአር. ግድያ የተመለከቱ ሰነዶችንም ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።