ፑቲን እና ትራምፕ በተጠባቂው የስልክ ውይይታቸው በምን ጉዳዮች ላይ ተነጋገሩ?
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል

የዩክሬን ጦርትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ የውይይታው አካል ነበር
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚ ፑቲን በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ተነግሯል።
ሁለቱ መሪዎች 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በፈጀ የስልክ ውይይታቸው የዩክሬን ጦርትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ የውይይታው አክል ነበር።
ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ ባደረጉት ውይይት በዩክሬን ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ዝርዝር እና ግልፅ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
ፑቲን እና ትራምፕ የዓለም ደህንነትን ለማረጋገጥ ካለባቸው ልዩ ኃላፊነት አንፃር ግንኙነታቸውን መደበኛ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል ብሏል ክሬምን በመግለጫው።
የስልክ ውይይቱ በዋናነት በተለይ በዩክሬን ያለውን ጦርት በስምምነት ለመቋቸት አሜሪካ ባቀረበችው እቅድ እንዲሁም "የአሜሪካ-ሩሲያን ግንኙነትን ወደነበረበት መመለስ ላይ ያተኮረ እንደነበረ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ አስታውቀዋል።
ፑቲን ከትራምፕ ጋር ባደረጉት ውይይት በዩክሬን ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ እንደሆኑ ማሳወቃቸውንም ፔስኮቭ አስውቀዋል።
የ30 ቀናት የተኩስ ስምነት እንዲደረስ እና በዩክሬን ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ለኪዬቭ የሚደረገው የውጪ ወታደራዊ እና የመረጃ ድጋፍ ሙሉ በመሉ መቆሙ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ መሆኑንም የክሬምሊን ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።
ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ ውይይታው የሁለቱ ሀገራ ግኙነትን ማሻሻ ላይ መወያየታቸውን ደግሞ ዋይት ኃውስ አስታውቋል።
በአሜሪካ እና ሩሲያ መካከል ያለው የተሻሻለ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትልቅ ጥቅም እንዳለው መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል ገልጿል።
የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት “በርካታ የኢኮኖሚ ስምምነቶችን” እንዲሁም ከሰላም ጋር ተያይዞ ጂኦፖለቲካዊ መረጋጋትንም ያስገኛል ሲል አክሏል።
ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ በኋላ በሁለቱ ፕሬዚዳንቶች መካከል ይፋዊ የስልክ ውይይት ሲደረግ ይህ ሁለተኛው ነው።
በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የመጀመሪያው የተካሄደው በየካቲት ወር እንደነበረ ይታወሳል።
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ከፑቲን ጋር ያላቸውን መልክ ግኙነት በመጠቀም ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ በ24 ሰአት ውስጥ ማቆም እንደሚችሉ መናገራቸው ይታወሳል።
ትራምፕ ወደ ኋይት ሀውስ ከተመለሱ በኋላ በፈረንጆቹ በ2022 በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት እልባት እንዲያገኝ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል።