ጾታቸውን ያስቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ በሚል ተላልፎ የነበረው ውሳኔ በፍርድ ቤት ተሻረ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጾታቸውን ያስቀየሩ ዜጎች የሀገሪቱን ጦር እንዳይቀላቀሉ የሚከለክል ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል

ፍርድ ቤቱ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ በጊዜያዊነት ማገዱ ተገልጿል
ጾታቸውን ያስቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ በሚል ተላልፎ የነበረው ውሳኔ በፍርድ ቤት ተሻረ
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ጠንካራ ፍትህ ስርዓት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች በፍርድ ቤት እየተሸሩ ይገኛል፡፡
ፕሬሬዳንት ትራምፕ ስልጣን በያዙ በሳምንቱ ነበር በተፈጥሮ ያገኙትን ጾታ የስቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ ትዕዛዝ ያስተላለፉት፡፡
ይህን ውሳኔ ተከትሎም 20 ጾቸውን ያስቀየሩ አሜሪካዊ ዜጎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ሲሆን በትናንትናው ዕለትም የፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔ የሀገሪቱን ህገ መንግስት የሚጥስ ነው በሚል በፍርድ ቤት ተሽሯል፡፡
የአሜሪካ ህገ መንግስት ዜጎች ጾታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ መገለል እና ሌሎች ተጽዕኖዎች ሊደርስባቸው እንደማይገባ ይደነግጋል ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ጦር በበኩሉ ከየካቲት ወር ጀምሮ ጾታቸውን ያስቀየሩ ዜጎች የሀገሪቱ ጦር አባል ሆነው ማገልገል እንደማይችሉ አሳውቆም ነበር፡፡
በቅርቡም ጾታቸውን ያስቀየሩ እና የአሜሪካ ጦር አባል የሆኑ ወታደሮችን ማባረር ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ውሳኔው በፍርድ ቤት መሻሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማስቀየር ይግባኝ እንደሚል ገልጿል፡፡
አሜሪካ ካሏት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ወታደሮች ውስጥ 15 ሺህ ያህሉ ጾታቸውን ያስቀየሩ ናቸው ተብሏል፡፡