62ኛው የግራሚ አዋርድ ድምፃዊት ቤሊ ኤሊሽን አንግሷል፡፡
በ84 ዘርፎች እጩዎች የቀረቡበት 62ኛው የግራሚ አዋርድ ትናንት ምሽት በሎስአንጀለስ ሲካሄድ አሜሪካዊቷ ድምፃዊት ቤሊ ኤሊሽ በአምስት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግባለች፡፡
የ18 ዓመቷ ድምፃዊት በምርጥ ጀማሪ አርቲስት፣ በዓመቱ አልበም፣በዓመቱ ዜማ፣ በምርጥ ነጠላ ዜማ እና ምርጥ የፖፕ ቮካል አልበም ዘርፍ አሸናፊ ሆናለች፡፡ በግራሚ ታሪክ ‘ዌን ዊ ኦል ፎል ኤስሊፕ ዌር ዱ ዊ ጎ’ በተሰኘው ስራዋ የዓመቱ አልበም ዘርፍን በ18 ዓመት ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ድምፃዊት ሆናለች፡፡
ከዚህ ቀደም በ20 አመቷ የዘርፉን ሽልማት በማግኘት ሪከርድ የያዘችው ቴይለር ስዊፍት ነበረች፡፡
ቤሊ ኤሊሽ በተጨማሪም በቀዳሚ አራት ዘርፎች ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴትና ሁለተኛዋ አርቲስት ሆናለች፡፡ በዘንድሮው ግራሚ አዋርድ በቅርቡ በሞት የተለየውን ትውልደ ኤርትራዊ ራፐር ኒፕሲ ሃስልን ለመዘከር ድምፃዊያን የኤርትራን ባህል ልብስ በመልበስ በመድረክ ስራቸውን አቅርበዋል፡፡
ትልቅ ግምት ተሰጥቶት የነበረውና በ8 ዘርፎች እጩ በመሆን ሲመራ የነበረው ሊዞ በሶስት ዘርፎች ሽልማት ወስዷል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን