የጋምቢያው ፕሬዘዳንት አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መሰረቱ
የጋምቢያው ፕሬዘዳንት አዳማ ባሮ ቀጣይ ምርጫዎች ላይ ያለእንቅፋት ለመወዳደር አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረታቸውን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በፊት ከነበሩበት የሀገሪቱ ትልቅ ፓርቲ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በመበላሸቱና ከስልጣን እንዲወርዱ ጥያቄ መብዛቱን ተከትሎ እራሳቸው የሚመሩትን ናሽናል ፒፕልስ ፓርቲን አቋቁመዋል፡፡
ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮ 2016 ላይ የቀድሞውን መሪ ያህያ ጃሜህን በማስወገድ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት በወቅቱም ጥምር የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ አድርገውላቸው ነበር፡፡
ባለፉት ጊዜያት ግን የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበረችው ጋምቢያ ፕሬዘዳንቱ ስልጣን ይልቀቁ አይልቀቁ በሚሉ ሀሳቦች ስትናወጥ ቆይታለች፡፡ የሀገሪቱ የምርጫ ህግ ለአንድ መሪ 5 ዓመታት የስልጣን ቆይታን ይፈቅዳል፡፡
ፕሬዘዳንት አዳማ ባሮ አዲስ ፓርቲ ማቋቋም የፈለጉትም በቀጣይ ምርጫ የየትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ድጋፍ ሳይጠይቁ ለመሳተፍ ነው፡፡