በአውስትራሊያ ሰደድ እሳት እስካሁን 24 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተዘገበ፡፡
በአውስትራሊያ መስከረም ወር የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት አሁንም በቁጥጥር ስር አልዋለም፡፡
እስካሁን በሰደድ እሳቱ ቢያንስ 24 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከ1200 በላይ ቤቶች በእሳቱ ሲወድሙ በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት መጋየቱ ተነግሯል፡፡ ሀገሪቱ ከሚገኙ እንስሳት ውስጥም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
የደረሰውን ውድመት ታሳቢ በማድረግም የሀገሪቱ ኮሜዲያን ሰለስተ ባርበር አርብ እለት ባደረገችው የፌስቡክ ቅስቀሳ 20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተሰብስቧል፡፡
በተለይ ደግሞ የኒው ሳውዝ ዌልሷ ከተማ ኮማ ቅዳሜ ማምሻውን የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት ይጓዝ የነበረ በሚሊዮን ሊትር የሚለካ ውሃ የጫነ ታንከር ፈንድቶ፣ ውሀውን ወደስፍራው ማድረስ ባለመቻሉ፣ እሳቱ ይበልጥ ተቀጣጥላለች፡፡
የሀገሪቱ ዋና ከተማ ካንቤራም ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ በማስተናገዷ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በከተማዋ የአየር በረራም ተቋርጧል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን 3000 ባላትን ያካተተ ተጠባባቂ የጦር ሀይል እንዲዘጋጅ አድርገዋል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ