ኬክ የመብላት ውድድር ላይ የተሳተፉት አውስትራሊያዊት ህይወት አለፈ፡፡
የመጀመሪያቹ አውሮፓውያን አውስትራሊያ የገቡበትን ብሄራዊ ቀን አውስትራሊያውያን በየአመቱ የምግብ ውድድርን አካተው ያከብራሉ፡፡
በዚሁ ክብረ በዓል ስማቸው ያልተጠቀሰው የ60 ዓመት ተወዳዳሪ ታዲያ ባህላዊ የሆነውን ቸኮሌትና ኮኮናት የተቀላቀለበት ለስላሳ ኬክ በብዛት የመብላት ውድድርን ይጀምራሉ፡፡
ነገር ግን ግለሰቧ ብዙም ሳይቆዩ የተጨነቀ ፊት በማሳየታቸው የዝግጅቱ አስተባባሪዎች አምቡላንስ ጠርተው ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ግለሰቧ ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም፡፡ በውድድሩ ወቅት ማወራረጃ ውሃ አለመያዛቸው ለመታነቃቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡
ዝግጅቱ የተካሄደበት ዘ ቢች ሀውስ ሆቴል በፌስቡክ ገፁ የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
አሸናፊዎች ሽልማት የሚረከቡበት የኬክ መብላት ውድድር የአውስትራሊያ ብሄራዊ ክብረ በዓል ቀን አንዱ ድምቀት ነው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ