65 ዓመታትን አንድ ላይ የኖሩ ጥንዶች አረፉ
የ86 ዓመቱ አዛውንት ጃክ ማሪሰን እና የ83 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ባለቤታቸው ሀሪየት ማሪሰን ከቀናት በፊት ጥር 2 በሰዓታት ልዩነት ነው ያረፉት፡፡
በሴንት ሉዊስ የህክምና ክትትል ላይ እንዳሉ ጃክ ህይወታቸው ባለፈ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ባለቤታቸውም ተከትለዋቸዋል፡፡
ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፍቅር እንዲለዋወጡ ነርሶቹ አልጋቸውን አገናኝተውላቸው ነበር እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፡፡ ፍቅር እስከመቃብር ይሏል እንግዲህ ይህ ነው፡፡