በሪዮ ዲ ጄኔሮ በፖሊስ የሚፈፀሙ ግድያዎች እየጨመሩ መምጣታቸው ተገለፀ
ከ1998 ጀምሮ በተደረገ የመዝገብ ምልከታ በ2019 በብራዚሏ ሪዮ ዲ ጄኔሮ ከተማ 1 ሺ 810 ሰዎች በፖሊስ መገደላቸው ተነግሯል፡፡ ይህም በቀን በአማካይ 5 ሰዎች ይገደላሉ እንደማለት ነው፡፡
ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ወንጀለኞችን ለመከላከል ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ ሀይላትንና እንደ ስናይፐር ያሉ መሳሪያዎችን ሀገሪቱ እንድትጠቀም ያስቻላትን ፖሊሲ ብዙዎች ወቅሰዋል፡፡
የመንግስት ሀላፊዎች በበኩላቸው ድርጊቱ ወንጀልንና ወንጀለኞችን ለመከላከል በአግባቡ ሲተገበር እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ሪዮ ዲ ጄኔሮ በብራዚል ካሉ ወንጀል ከሚበዛባቸው ከተሞች አንዷ ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ትልቁ የከተማዋ ፈተና ነው፡፡
ባለፈው ዓመት የከተማዋ አስተዳደር ሆነው ወደ ስልጣን የመጡት የቀድሞው የሀገሪቱ ዳኛና የባህር ሀይል ዊልሰን ዊትዘል፣ ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር እስከ ግድያ የሚደርስ አቋም ይዘው በመምጣታቸው በፀጥታ አስከባሪዎች የሚወሰድ ጥቃት ጨምሯል ተብሏል፡፡
2019 ላይ የተመዘገበው ግድያ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ18 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ከ1991 ወዲህ ለመጀመሪ ጊዜ ራስን የማጥፋት ወንጀል ባለፈው አመት በ20 በመቶ መቀነስ አሳይቷል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ