በመስከረም 27 2017 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ስንት ብር ገባ?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ112 ብር እየገዛ፤ በ123 እየሸጠ ይገኛል
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 112 ብር እየገዙ፤ እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ መስከረም 27 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን ከመደበኛው የምንዛሬ ዋጋ ላይ እስከ 16 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወቃል።
ባንኩ በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.9585 ብር እየገዛ በ127.0783 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።
እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።
በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.4804 ብር እየገዛ በ125.9781 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።