ቫይረሱን ለመከላከል ኤርትራ አራት መመሪያዎችን አወጣች
እስካሁን ኮሮና ቫይረስ ያልገባበት ኤርትራ በጣም አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር ዜጎች የውጭ ጉዙ እንዲሰርዙ አሳስባለች
የኮሮና ቫይረስን ከወዲሁ ለመከላከል ኤርትራ አራት መመሪያዎች አወጣች
የኮሮና ቫይረስን ከወዲሁ ለመከላከል ኤርትራ አራት መመሪያዎች አወጣች
ኤርትራ የኮሮና ቫይረስን አስከፊነት በመገንዘብ ተጓዦች መከተል አለባቸው ያለቻቸውን አራት መመሪያዎች ማውጣቷን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
መመሪያው በዋናነት የሚያተኩረው ወደ ኤርትራ የሚመጡና ከኤርትራ ወደ ውጭ የሚሄዱ ተጓዦች ላይ መሆኑ ገልጿል፡፡
ምንምእንኳን እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ ባይከሰትም፣ የኤርትራ የጤና ሚኒስቴር አራት መመሪያዎችን ለሁሉም ዜጎችና በሀገሪቱ ለሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች አውጥቷል፡፡
በጣም አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ሰው ከውጭ ጉዞ መቅረት፤ ሁሉም ሰው ህዝብ በሚበዛበት ቦታ አለመሄድ፣ ከኤርትራ ወደ ውጭና ከውጭ ወደ ኤርትራ የሚደረግ ጉዞ መቀነስ አንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ሁኔታዎች እየተከታተለ አስፋላጊ ሲሆን ተጨማሪ መመሪያ ያወጣል የሚሉት አራቱ መመሪያዎች ናቸው፡፡
ኮሮና ቫይረስና ምስራቅና አፍሪካ
ኮሮና በምስራቅ አፍሪካ አድማሱን አስፋፍቶ እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን፣ በኬንያ፣ በታንዛኒያና በሶማሌያ መግባቱ ተረጋግጧል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መጋቢት 4፣ 2012 በሰጡት መግለጫ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩን ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መጋቢት 4፣ 2012 በሰጡት መግለጫ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩን ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ግለሱቡ ጃፓናዊ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የካቲት 25 መሆኑንና ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸው 25 ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረስ ተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሲደርስ፣ በለይቶ ማቆያ ቦታ ደግሞ 117 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ከቻይና ውሀን ግዛት የተነሳው የኮሮና ቫይረስ መላው ዓለምን አዳርሷል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን ከ5,000 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን 170,000 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡