የገቢዎች ሚኒስቴር ኢ-ታክስ አገልግሎትን ለማስፋፈት ወጥኗል
የገቢዎች ሚኒስቴር እስከ ታህሳስ 30 /2012 ዓ.ም ድረስ 10 ሺ ግብር ከፋዮችን ወደ ኢ ታክስ አገልግሎት ለማስገባትም እየሰራሁ ነው አለ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግብር ከፋዮች ኢንተርኔትን በመጠቀም ታክስን የማስታወቅ፣ ክፍያን የመፈፀም፣ የክሊራንስ አገልግሎት የማግኘት እና የታክስ ነክ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎች ለማግኘት የሚረዳ የኢንተርኔት አሰራር ‹‹የኢ-ታክስ›› አገልግሎት ጀምሯል፡፡
በዚህም መሰረት ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት፣ ከምስራቅ እና ምዕራብ አነሰተኛ ግብር ከፋች ቅንጫፍ ጽ/ቤት ለተወጣጡ ግብር ከፋዮች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ከታህሳስ 13 ጀምሮ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው ኢ-ታክስ የሚያጠቃልላቸው የአገልግሎት አይነቶች፣ አንድ ግብር ከፋይ ለኢ-ታክስ ምዝገባ ማሟላት የሚጠበቅበት ቅድመ ሁኔታዎች፣ ኢ-ታክስ መመዝገብ ያለበት ግብር ከፋይ ማን ነው፣ አንድ ግብር ከፋይ የኢ-ታክስ ተመዝጋቢ በመሆኑ የሚያገኛቸው ጥቅሞች እና ስለ ኢታክስ፣ ኢ ፋይሊንግና ኢፔይመንት አጠቃቀምን በተመለከተም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በለሙያዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ባንኩ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኢፔይመንት አማካኝነት እንዲከፍሉ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የተለያዩ እገዛዎችንም ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተፈራ ደግፌ ቅርንጫፍ የቢዝነስ ማናጀር የሆኑት አቶ ክፍሉ ልሳነወርቅ ገልጸዋል ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያትተው፡፡