የአውሮፓ ህብረትና ቱርክ የስደተኞች ችግርን ለመፍታት በሚውለው በጀት ጉዳይ ላይ ተፋጥጠዋል
የአውሮፓ ህብረትና ቱርክ የስደተኞች ችግርን ለመፍታት በሚውለው በጀት ጉዳይ ላይ ተፋጥጠዋል
የአውሮፓ ህብረት ከሶሪያ፣ከኢራቅ፣ከአፍጋኒስታንና ከእነዚህ ሀገራት ውጭ ወደ አውሮፓ የሚጎርፉትን ስደተኞች ለማስቆም ከቱርክ ጋር ስምምነት ለመፈረም እየተሯሯጠ መሆኑን ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡
ነገርግን ቱርክ ከብራሰልስ የቀረበውን ጥሪ ለመቀበል ያላትን ዝግጁነት የሚያሳይ ምልክት የለም፡፡
እ.ኤ.አ በ2016 ቱርክ ስደተኞችን በግዛቷ ውስጥ ለማስቀረት ከህብረቱ ጋር ተስማምታ ነበር፡፡ ቱርክ ስምምነቱን ለመጣስ የተገደደችው የአውሮፓ ህብረት ቃል የገባውን የገንዘብ ድጋፍ ባለማድረጉ ነው፡፡
የአውሮፓ ህብረት ውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሼፍ ቦሬል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የችግሩን መጠን ለመገምገም በዛግሬብ በተሰባሰቡበት ወቅት እንደተናገሩት አባል ሀገራት በ2016 ቃል ገብተው ከነበሩት ስድስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው ብለዋል፡፡
ነገርግን አራት ሚሊዮን ስደተኞችን እያስተናገደች ያለችው ቱርክ ገንዘቡን ለማግኘት መጀመሪያ ወደ አውሮፓ የሚፈልሱትን ስደተኞች ማስቆም አለባት ብለዋል ቦሬል፡፡
ቦሬል ያምቢሆን ቱርክ ስደተኞችን እንደጫና መፍጠሪያ መጠቀም የለባትም ብለዋል፡፡
ህብረቱ ብዙ ገንዘብ ለመስጠት ቢወስንም የቱርክን ፍላጎት ለማሟላት መብቃቱ ወይንም አለመብቃቱ ግልጽ አይደለም፡፡