የቀድሞው የግብፅ ፕሬዘዳንት ሁስኒ ሙባረክ በ91 አመታቸው ሞቱ
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዘዳንት ሁስኒ ሙባረክ በ91 አመታቸው ሞቱ
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዛዳንት ሁስኒ ሙባርክ ዛሬ መሞታቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል፡፡
ሁስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2011 በግብፅ ዋና ከተማ በታህሪር አደባባይ ለ18 ቀናት የቆየውን ህዝባዊ አመፅ ተከትሎ ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ሙባረክ ግብፅን ለ30 አመታት ያህል ያለተቀናቃኝ መምራት ችለው ነበር፡፡
በህዛባዊ አመፅ ከስልጣን ከለቀቁ በኋላ ለበርካታ አመታት የታሰሩት ሙባረክ እ.ኤ.አ. በ2017 ከቀረቡባቸው በርካታ ክሶች ነፃ ተብለው ተለቀው ነበር፡፡