ቢሊየነሩ ወደ ጨረቃ ለሚያደርገው ጉዞ ያቀረበውን የአጋር ጥያቄ ሰረዘ፡፡
ጃፓናዊው ቢሊየነር ዩሳኩ ማኢዛዋ ከ20 ዓመት በላይ የሆነች አጋር እንድትኖረውና ወደ ጨረቃ በሚያደርገው ጉዞ አብራው እንድትጓዝ በማህበራዊ ድረ-ገፁ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ 28 ሺ የሚሆኑ ሴቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ይሁን እንጂ የፋሽን ዲዛይን ኢንደስትሪ ውስጥ የተሰማራው ግለሰብ የተለያዩ ስሜቶች ስለተሰሙኝ ጥያቄዬን አንስቻለሁ ብሏል፡፡
በትዊተር ገፁ ላይም ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ መልስ ለሰጣችሁኝ ሁሉ አመሰግናለሁ በመጨረሻው ውሳኔዬም ተፀፅቻለሁ ብሏል፡፡
የ44 ዓመቱ ባለሀብት ከዚህ ቀደም ከ27 ዓመቷ ተዋናይት አያሜ ጎረኪ ጋር የነበረውን የትዳር ግንኙነት አቋርጧል፡፡
በማህበራዊ ድረ-ገፆች ትኩረት የሚስቡ ጥሪዎችን ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በትዊተር ገፁ ካሰፈራቸው ፅሁፎች አንዱን ለተጋሩ 100 ሰዎች 925 ሺ ዶላር እንደሚሰጥ በማሳወቁ ፅሁፉ በርካቶች የተጋሩት ሆኖ አልፏል፡፡
ምንም እንኳን የአጋር ጥያቄውን ቢሰርዘውም ወደ ጨረቃ የሚያደርገው ጉዞ ግን ለ2023 ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ይህም ከተሳካ ከ1972 ወዲህ ጨረቃን የረገጠ የመጀመሪያው ግለሰብ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ-ዘ ጃፓን ታይምስ