የ2019 ዋና ዋና የህክምና ቴክኖሎጂ ግኝቶች የትኞቹ ናቸው?
በ2019 በህክምናው ዘርፍ የተገኙ አበይት የቴክኖሎጂ ግኝቶች
የጡት ካንሰርን ለመለየት የሚያስችል የደም ምርመራ
በእንግሊዝ ኖተንግሀም ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች የጡት ካንሰር ምልክቶች ከመታየታቸው አምስት አመት ቀድሞ ችግሩን በደም ምርመራ መለየት የሚያስችል ህክምናን አስተዋውቀዋል፡፡የደም ምርመራው ጊዜና ወጪን የሚቆጥብ ሲሆን ተጨማሪ ጥናቶች ተደርገው ስኬታማ ከሆን በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
የመርሳት በሽታ/አልዛይመር መድሀኒት
ተመራማሪዎች አዱካኑማብ የተሰኘውን መድሀኒት በሙከራ ደረጃ ለ 18 ወራት የተጠቀሙ ሰዎች ከ15-27 በመቶ ለውጥ አሳይተዋል ብለዋል፡፡ መድሀኒቱ ወደ ገበያ ከመግባቱ በፊት ፈቃድ እንዲሰጠው በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ክሪስፕር
ዘረ-መልን እና ዲ ኤን ኤ ን ለማሻሻል የሚረዳው ክሪስፐር ቴክኖሎጂ በ2019 ነው በሙከራ ደረጃ የተዋወቀው፡፡ ቴክኖሎጂው ለህክምና እና ለሰብል ዝርያዎች ምርምር የሚውል ነው፡፡ በተለይም የሰብል ተባዮችንና ወባን ለማጥፋ እንዲሁም ኤች አይ ቪን ለማከም ያግዛል ተብሏል፡፡
ሮቦቲከ ሰርጀሪ
የህክምና ባለሞያች ከባድ ቀዶ ህክምናን በሚያከናውኑበት ጊዜ ሮቦቶች የታካሚዎችን የጤና ሁኔታ በመረዳት ተጨማሪ መረጃ ለባለሞያዎቹ የሚያቀብሉበት አሰራር ነው፡፡ ነገር ግን ከድጋፍ መስጠት ወደ ሙሉ ህክምና ሰዎችን ተክተው ሊገቡ ይችላሉ በሚል ተገልጋዮች ስጋት ያነሳሉ፡፡
ሰው ሰራሽ የውስጥ አካላት
ተመራማሪዎች በሰውነት ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮችን ኦቫሪና ጣፊያንም ጭምር በሰው ሰራሽ መንገድ አዘጋጅተው ሰውነት ውስጥ በማስገባት እዚያው አድገው የታመመውን አካል እንዲተኩ አድርገዋል፡፡ ይህም ለታካሚዎች እረፍት ከመስጠቱ ባለፈ ንቅለ ተከላ ለሚያደርጉ ሰዎች መፍትሄ ይሆናል ተብሏል፡፡
ቴሌ ኸልዝ
የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች በዲጂታል መገልገያዎች በሚገጠም መተግበሪያ አማካኝነት የግል መረጃቸው ተጠብቆ የህክምና ባለሞያችን ፊት ለፊት ሳያገኙ ህክምና የሚያገኙበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይ ለከባድ ህመምተኞች ጥሩ አማራጭ ነው ተብሏል፡፡
ገመድ አልባ የአእምሮ ሴንሰር
በሰዎች አንጎል ውስጥ ያለውን ሙቀትና ጫና ለመለካት ወደ አንጎል የሚገቡ መሳሪያች ሲሆኑ ህክምናው ካለቀ በኋል ተጨማሪ ቀዶ ህክምና ሳይደረግ እዛው መሟሟት የሚችሉ ናቸው፡፡
3ዲ ፕሪንት
3ዲ ፕሪንት እንደ ልብና ሌሎች የሰውነት አካላትን በማተም እንደ አዲስ ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የንቅለ ተከላ ስራን ለማቃለል ይረዳል ተብሏል፡፡