ከነገ ጥር 05/2012 ዓ.ም ጀምሮ የዊንዶው-7 አገልግሎትን እንደሚያቋርጥ ማይክሮሶፍት ኩባንያ አስታውቋል፡፡
ለዊንዶው-7 የሚሆኑ ማናቸውንም ዓይነት የደህንነት መጠበቂያና ማዘመኛ አገልግሎቶቹን እንደሚያቋርጥ ያስታወቀው ኩባንያው፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የዊንዶው ምርቶቻቸውን ሊያዘምኑ የሚችሉባቸውን አዳዲስ አማራጮች ስለመፍጠሩም ነው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በፌስቡክ ገጹ ያስነበበው፡፡
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ዊንዶው-7ን ወደ ዊንዶው-10 እንዲቀይሩም ኩባንያው አሳስቧል፡፡
ይህን ለማያደርጉ አካላት ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጥር 06/2012 ዓ.ም ጀምሮ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ድጋፍ እንደማያደርግም ነው ማይክሮሶፍት ያስታወቀው፡፡
ተጠቃሚዎቹ ዊንዶው-10ንን እንዲጭኑ ለማድረግ የሚያስችል ማስታወሻ የሚሆኑ ማንቂያዎችን ማሳየት እንደሚጀምርም ገልጿል፡፡
ዊንዶው-7ንን በዊንዶው-10 መተካት የሚፈልጉ አካላትም ተከታዮቹን መንገዶች በመጠቀም በነጻ ማዘመን ይችላሉም ተብሏል
1. በመጀመሪያ ይህን አያያዥ https://www.microsoft.com/en-us/software-download/windows10 በመጫኝ መክፈት
2. በመቀጥል 'Download Tool now' የሚለውን መጫን
3. የሚዲያ ክሬሽን ቱልን በመክፈት /agree to the license/ የሚለውን መምረጥ
4. ይህን ፒሲ/ PC/ አሁን ያሻሽሉ የሚለውን አማራጭ ይምረጡ እና ቀጥል /Next/ን ጠቅ ያድርጉ
5. ሁሉንም መተግበሪያዎች እና ፋይሎች አቆይ የሚለውን ይምረጡ እና መቀጠል፡፡ ከዚያ የዊንዶውስ ኢንስቶል /Install/ የሚለውን በተን/button/ በመጫን ሂደቱን ማስጀመር
6. ዊንዶው-10ን በሚጭኑበት ወቅት ኮምፒተርዎ ብዙ ጊዜ እንደገና ስለሚጀምር/ restart/ እና ሂደቱ ትንሽ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል በትእግስት መጠበቅ ይኖርቦታል፡፡
7. ዊንዶውስ 10 መጫኑን ካጠናቀቀ እና ከተገናኙ በኋላ የዊንዶውስ-10 ትክክለኛነት ማረጋገጥ Settings > Windows Update > Activation/ የሚሉትን እንደቅደም ተከተሉ በመምረጥ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
ማይክሮሶፍት ይህንን ነፃ የማሻሻያ ዘዴ መቼ እንደሚዘጋ ስለማይታወቅ ነፃ የዊንዶውስ-10 ቅጂዎን ማጣት የማይፈልጉ ከሆነ በፍጥነት መተግበር ይገባዎታል፡፡
ምንጭ፡- ኢንሳ