ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ አየር ጥራትም ተለክቶ ነበር
የናይሮቢ የአየር ጥራት ይለካል
የዘንድሮውን ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና በኬንያ ናይሮቢ ከመካሄዱ በፊት ውድድሩ በሚካሄድበት አካባቢ ያለው የአየር ጥራት እንደሚለካ የዓለም አትሌቲክስ ተቋም አስታውቋል፡፡
ባለሙያዎቹ ፈረንሳይ ሞናኮ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ትናንት ኬንያ መግባታቸውን ያስታወቀው ተቋሙ “ኩናክ” የተሰኘ የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ ሻምፒዮናው በሚካሄድበት የካሳራኒ ስታዲየም መተከሉንም ገልጿል፡፡
መሳሪያው ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ተተክሎ ነበር፡፡
ይህን ያስታወሰው ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ የናይሮቢው የታዳጊዎቹ ሻምፒዮና የአየር ጥራት የሚለካበት የመጀመሪያው ዓለም ቀአፍ ውድድር መሆኑን ዘግቧል፡፡
ሻምፒዮናው በመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ የሚካሄድ ነው፡፡
ኬንያ ከሶስት ዓመታት በፊት በዚሁ በካሳራኒ ስታዲየም ከ17 አመት በታች የዓለም ሻምፒዮናን ማስተናገዷ የሚታወስ ነው፡፡