በዩክሬን አይሮፕላን ቦይንግ 737 አደጋ በበብዛት የሞቱት ኢራናውያንና ካናዳውያን ናቸው
176 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የዩክሬን ዓለማቀፍ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ፕሌን ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ማለዳ ላይ ከቴህራን አየር ማረፊያ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ተከስክሶ ያሳፈራቸው ሰዎች በሙሉ በአደጋው መሞታቸው ይታወቃል፡፡ በአደጋው የሞቱት በቀጣዩ የመረጃ ምስል የተጠቀሱ የ 7 ሀገራት ዜጎች ናቸው፡፡