በ19ኛው ክፍለዘመን የተሰረቀው የብር “አውራዶሮ” ወደ ናይጀሪያ ሊመለስ ነው
እ.ኤ.አ. በ19ኛው ክፍለዘመን በእንግሊዝ ወታደሮች የተሰረቀውና በኋላም በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ለጀሰስ ኮሌጅ የተሰጠው የብር “አውራዶሮ” ወደ ሀገሩ ናይጀሪያ ሊመለስ መሆኑን ሲኤን ኤን ዘግቧል፡፡
ቅርሱ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ የንጉሳውያን ንብረት መሆኑንና እ.ኤ.አ. 1897 በቀድሞዋ ቤኒን በአሁኗ ናይጀሪያ በወረራ ዘመቻ መዘረፉን ኮሌጁ ገልጿል፡፡
የምሁራን፣ የአክቲቪስቶችና የተማሪዎች ቡድን በመተባበር ኮሌጁ ከባሪያ ንግድ ጋር ያለውን ግንኙነት ለመዳሰስ ሲሰሩ ነበር፡፡ የቅርሱን መነሻ ለመወሰን የቡድኑ አባላት ከቤኒን ዲያሎግ ግሩፕ ጋር ላለፉት ለሦስት አመታት ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡
እ.ኤ.ኤ.በ1905 ቅርሱ በአንድ የተማሪ አባት አማካኝነት ለእንግሊዙ ኮሌጅ ተሰጠ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016 ኦኩኮር እየተባለ የሚጠራው ይህ ቅርስ ተማሪዎች ወደ ናይጀሪያ እንዲመለስ መጠየቃቸውን ተከትሎ ከኮሌጁ አዳራሽ እንዲነሳ ተደርጎ ነበር፡፡
ቅርሱን የመመለስ ውሳኔ ታሪክን የማጥፋት ሳይሆን ከቅርስ ጥበቃ ቡድኑ ጠንካራ ስራ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጀሰስ ኮሌጅ ኃላፊ ሶኒታ አለይኔ ገልጸዋል፡፡ ከጥልቅ ምርምር በኋላና የቅርስ ቡድኑ በታታሪነት ስራወችን በመስራት የቅርሱን መነሻ መፈለግ ወሳኝ መፍትሄ እንደነበረ ሶኒታ አለይኔ ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ኮሌጁ ቅርሱ መቼ እና በምን ሂደት እንደሚመለስ በግልጽ አላስቀመጠም፡፡
እ.ኤ.አ በ19ኛው ክፍለዘመን የእንግሊዝ ጦር የቤኒንን ግዛት ከወረሩ በኋላ የብር ቅርሶችን መዝረፍ ችለው ነበር፡፡ ቅርሶቹ በተለያዩ የምእራባውያን ሙዚየሞች ሲሸጡ እንደነበረና የናይጀሪያ መንግሰት እ.ኤ.አ. በ1960 ጀምሮ ቅርሶቹ እንዲመለሱ ሲጎተጉት ቆይቷል፡፡
ባለፈው አመት የሎንደኑ የእንግሊዝ ሙዚየም የተወሰኑ ቅርሶችን በጊዜያዊነት ወደ ቤኒን የንጉሳውያን ሙዚየም መልሶ ነበር፡፡