2 ሚሊዮን የሆንግኮንግ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረት ተጋልጠዋል ተባለ
በቻይናዋ ራስ ገዝ አስተዳደር ሆንግኮንግ በአዋቂ የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች አንድ ሶስተኛ ወይም 2 ሚሊዮን የሚሆኑት ከመጥፎ አጋጣሚ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ ከባድ የአዕምሮ ውጥረት መጋለጣቸውን አንድ ጥናት ይፋ አድረገ፡፡
የሆንግኮንግ ዩንቨርሲቲ ተመራማዎች ከፈረንጆቹ 2009-2019 በ18 ሺ ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት 32 በመቶ የሚሆኑት የችግሩ ምልክት ታይቶባቸዋል፡፡ የአዕምሮ ውጥረቱ እንቅልፍ ማጣት፣ ምቾት ያለመሰማትና ቅዠት መገለጫዎቹ ናቸው፡፡
ረጅም ጊዜ በወሰደው ጥናት 2015 ላይ 5 በመቶ ብቻ የነበረው የችግሩ ተጋላጮች ቁጥር 2019 ላይ ወደ 32 በመቶ ማሻቀቡ ተመላክቷል፡፡
በሆንግኮንግ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ለአዕምሮ ውጥረቱ በብዛት መከሰት አንዱ ምክንያት ሆኗል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን