ሩሲያ በአንድነት ስትቆም “አትበገርም” ፡ የፑቲን የድል በዓል መልእክት
በ75ኛው የድል በዓል ላይ ፕሬዘዳንት ፑቲን “የቀድሞ አርበኞቻችን ሞትን በመጋፈጥ ሲዋጉ ነበር” ብለዋል፡፤
ፕሬዘዳንት ፑቲን ሩሲያ በአንድነት ስትቆም “አትበገርም” ሲሉ የ75ኛውን የድል በዓል መልእክት አስተላለፉ
ፕሬዘዳንት ፑቲን ሩሲያ በአንድነት ስትቆም “አትበገርም” ሲሉ የ75ኛውን የድል በዓል መልእክት አስተላለፉ
ሩሲያ በ2ኛው የአለም ጦርነት ወቅት የጀርመኑን ናዚ ወረራ ያሸነፈችበትን 75ኛ አመት ስታከብር የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያውያን በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በሬድ እስኩየር በወታደራዊ ትእይንት ይከበር የነበረው የድል በአል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከተራዘመ በኋላ ፑቲን “በአንድነት በምንቆምበት ጊዜ የማንበገር መሆናችንን እናውቃለን፤ እናምናለን”ሲሉ በቴሌቪዥን ተደምጠዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ፑቲን “የቀድሞ አርበኞቻችን ሞትን በመጋፈጥ ሲዋጉ ነበር፤ እኛም ከእነሱ ጋር እኩል የሆነ አንድነትና ብርታት ሁሌም ይኖረናል” ብለዋል፡፤
ዘንድሮው የታቀደው የድል በአል ፕሬዘዳንት ፑቲን በአለም መሪዎች ታጂበው 15ሺ ወታደሮች በሬድ እስኩየር የሚያሳዩትን ወታደራዊ ትእይንት እንደሚታደሙ ተገልጾ ነበር፡፡
ነገርግን የኮሮና ቫይረሳ በመላው አለም ተስፋፍቶ በመጨረሻም ሩሲያን ሲያጠቃ፣ ባለፈው ወር ክሬሚሊን ክብረበዓሉን ማካሄድ እንደማይቻል በመገንዘቡ ወደዚህ አመት መጨረሻ አስተላልፎታል፡፡
የድሉን ቀን ለሩሲያውያን ቅዱስ ቀን ነው ያሉት ፑቲን ትልቅ ህዝባዊ ዝግጅት ማካሄድ ለኮሮና ወረርሽኝ ያጋልጣል ብለዋል፡፡
ፑቲን ሶቬት ህብረት ታላቅ ለሀገር ፍቅር የተደረገ ጦርነት ብላ በምትጠራው ጦርነት መስዋትነት የከፈሉትን የሚያስታውስ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከክሬሚሊን አጥር ውጭ አበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡
የሀገሪቱን ወታዊ ኃያልነት የሚያሳዩ ወታደራዊ አውሮፕላኖችና ተዋጊ የጦር ጀቶችና መሞስከ ሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል፡፡