የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የአንድነት መንግሰት ለመመስረት ተስማምተናል አሉ
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞው አማፂ መሪ ሪክ ማቻር የሽግግር የአንድነት መንግስት ለመመስረት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምንምእንኳን ሁለቱ መሪዎች በመካካላቸዉ ያለውን ልዩነት ከተቀመጠው ቀነገደብ በፊት መፍታት ባይችሉም መንግሰት ለመመስረት መስማማታቸዉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በአሜሪካ ጫና ምክንያት ኪርና ማቻር ለአምሰት አመታት የዘለቀውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማቆምና ታህሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት ባለፈው አመት ተስማምተው ነበር፡፡
ነገርግን ሁለቱ መሪዎች የተቀመጠውን ቀነገደብ በ100 ቀናት መግፋታቸው፣ አሜሪካ ከሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ወዲህ ከፍተኛ የስደተኞች ችግር የፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ያገረሻል በሚል ስጋት አምባሳደሯን እንድትጠራ አስገድዷታል፡፡