የኦማን ሱልጣን ቃቡስ ቢን ሰኢድ በ79 ዓመታቸው አረፉ
በዓረቡ ዓለም በመሪነት ረዥም ጊዜ በመቆየት ወደር የሌላቸው ቃቡስ ቢን ሰኢድ አል ሰዒድ በ79 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ነው ያረፉት፡፡
ሱልጣኑ የካንሰር ታማሚ እንደነበሩ የተዘገበ ሲሆን ከወር በፊት በቤልጂየም ህክምና ሲከታተሉ ነበር ተብሏል፡፡
ሱልጣኑ እኤአ በ1970 ደም ሳይፈስ በእንግሊዝ ድጋፍ አባታቸውን ከስልጣን በመፈንቀል ነው ወደ መሪነቱ የመጡት፡፡
ቃቡስ ቢን ሰኢድ ኢራንን መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ሀገሪቱ ፈጣን እና ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባ ወደ ብልጽግናው ጎዳና አምርታለች፡፡
ኦማን ከአሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ጋር ጠንጃራ ወዳጅነት እንድትመሰርትም አድርገዋል፡፡ የአሜሪካ መንግስትም ሙስካት በሚገኘው ኤምባሲዋ አማካኝነት በ ሱልጣኑ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
በመሪዋ ሞት ሀገሪቱ 3 ብሄራዊ የሀዘን ቀናትን አውጃለች፡፡
ትዳርና ልጅ የሌላቸው ሱልጣን ቃቡስ ቢን ሰኢድ ወራሻቸውን ከህልፈታቸው በፊት ባያዘጋጁም፣ የቀድሞው የባህል እና ቅርስ ሚኒስትር ሀይሰም ቢነ ጧሪቅ በምትካቸው ተሹመዋል፡፡ ይሄም በኑዛዜያቸው መሰረት መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
ኦማን በአረብ ባህረ ሰላጤ ምስራቃዊ ጫፍ የምትገኝ ሀገር ስትሆን፣ የተባበሩት አረብ ኤሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የመን እና ኢራን ያዋስኗታል፡፡