የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አሳለፈ
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አሳለፈ
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመላው ዓለም አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቖጣጠር ያስችለናል ያሏቸውን የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለም ህዝብ በቤት ውስጥ መቆየትን ጨምሮ በተለያየ አይነት እገዳ ውስጥ ይገኛል፡፡
ዜጎቻቸው እና ሌሎች ነዋሪዎቻቸው ከቤት እንዳይወጡ ካገዱ ሀገራት መካከል የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ይጠቀሳል፡፡
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የወጡ የተለያዩ ህጎችን በሚጥሱ አካላት ላይ ከ500 ድርሀም እስከ 50,000 ድርሀም የሚደርስ ቅጣት ወስኗል፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ሀማድ ሰይፍ አል-ሻምሲ የቅጣት ዝርዝሮችን ያካተተውን ህግ ትናነት መጋቢት 20/2012 ዓ.ም ይፋ አድርገዋል፡፡
የጥሰት ዝርዝር እና የተጣሉ ቅጣቶች
በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ 723,000 በላይ ደርሷል፡፡ እስካሁን ከ 34,000 በላይ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ከ151,800 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል፡፡
በተጠቂዎች ቁጥር ከፊት ለፊት የተሰለፈችው ዩኤስ አሜሪካ ከ 140,000 በላይ ተጠቂዎች ይገኙባታል፡፡ በሟቾች ቁጥር ደግሞ እስከ ትናንት መጋቢት 20/2012 ዓ.ም ድረስ 11,000 ያክል ሰዎች ህይወት ያለፈባት ጣሊያን ስትመራ ስፔን ትከተላታለች፡፡
እስካሁን ክትባትም ሆነ ምንም አይነት መድኃኒት ያልተገኘለት ኮሮና ቫይረስ ዋነኛ መከላከያ መንገዱ በዓለም ጤና ድርጅት፣ በሀገራት የጤና ባለስልጣናት እና በመንግስታት የሚወጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መተግበር ነው፡፡