2019 አሜሪካ በታሪኳ ብዙ የጅምላ ግድያዎችን ያስተናገደችበት አመት ነው ተባለ
አሶሼትድ ፕረስ፣ ዩ ኤስ ኤ ቱደይ እና ኖርዝ ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባሰባሰቡት መረጃ በ2019 በአሜሪካ 41 የግድያ አጋጣሚዎችና 211 ሞት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
አስከፊ ተብለው የተለዩት ደግሞ በቨርጂኒያ ባህር ዳርቻ 12 ሰዎች የሞቱበትና በኤልፓሶ 22 ሰዎች የተገደሉባቸው አጋጣሚዎች ናቸው፡፡
ከ41ዱ የግድያ አጋጣሚዎች 33ቱ በጦር መሳሪያ የተፈጸሙ ናቸው፡፡ ካሊፎርኒያ ደግሞ 8 ነዋሪዎቿ የተገደሉባት ቀዳሚዋ ግዛት ሆናለች፡፡
መረጃው የተገኘበት ዳታ ቤዝ ከ2006 ጀምሮ በአሜሪካ የተፈጸሙ ግድያዎችን አቅርቧል፡፡ ነገር ግን የተደረገው ጥናት ከ1970 ጀምሮ ያሉትን የግድያ አጋጣሚዎች አካቶ ነው 2019ን በርካታ የግድያ አጋጣሚዎች የተከሰቱበት ዓመት ነው ያለው፡፡
በአሜሪካ ምንም እንኳን የራስ ማጥፋት ወንጀሎች እየቀነሱ ቢመጡም የጅምላ ግድያ አጋጣሚዎች መጨመራቸው በርካቶች ህይወታቸውን እንዲያጡ እያደረጋቸው ነው ተብሏል፡፡
ለዚህ ደግሞ በሀገሪቱ የመሳሪያ ባለቤትነት ህግና የመሳሪያ ቁጥጥር የላላ መሆን ምክኒያት ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ