በዓመት ከ33 ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር በቅርቡ ይጀመራል ተባለ
'ኢትዮጵያ ዩዝ ኮኔክት' የተሰኘው ሀገር አቀፍ የወጣቶች መርሃ ግብር የሚጀመረው በኢፌድሪ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ33 ሺ የሚልቁ ወጣቶችን በማገናኘት በጋራ የሚመክሩበትንና የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ዓላማ አለው ተብሏል፡፡
መርሃግብሩ በመጪው ታህሳስ 27/2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል በሚካሄድ ይፋዊ የመክፈቻ ስነ ስርዓት እንደሚጀመር ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፣ መርሃ ግብሩ፡-
የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ተወዳዳሪነታቸውን የማሳደግ
ወጣቶች በግጭት አፈታትና በሰላም እሴቶች ግንባታ ንቁ ተዋናይ እንዲሆኑ የማድረግ
በቴክኖሎጂ፣ ስርፀትና ምርምር መስኮች የወጣቶች ክህሎት ማሳደግ
ስብዕናው የተሟላ፣ሃላፊነት የሚሰማው ንቁ ወጣት የመፍጠር
የወጣቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነትና ትስስር የማሳደግ እንዲሁም ወጣቶቹን በማስተባበር
1 ሚሊዬን ችግኞችን የመትከል
የአቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን ቤት የመጠገንና ማገዝ
5 መቶ ሺ ዩኒት ደምን ከለጋሾች በመሰብሰብ መንግስትን 50 ሺ ዶላር ሊደርስ ከሚችል ወጪ የመታደግ
ዝርዝር ዓላማ እንዳለው ሚኒስቴር መ/ቤቱ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡