በአውስትራሊያ በተከሰተው ሰደድ እሳት የተጠረጠሩ 24 ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ
በአውስትራሊያ የተከሰተው ሰደድ እሳት በዋናነት በከባድ ሙቀትና ድርቅ የተከሰተ ቢሆንም ሆን ብለው እሳት በመለኮስ እጃቸው አለበት የተባሉ 24 ሰዎች ላይ የሀገሪቱ ፖሊስ ክስ መመስረቱን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ከህዳር ወር ጀምሮ በ183 ሰዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ቅጣቱ ከማስጠንቀቂያ እስከ ወንጀል ክስ የደረሰ መሆኑ ተነግሯል፡፡
24ቱ ተጠርጣሪዎች ሆን ብለው እሳት ለኩሰዋል አሊያም በቸልተኝነት የሲጋራ ቁራጭ ጥለዋል በሚል የተያዙ ናቸው፡፡
መስከረም ወር ላይ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት እስካሁን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አልዋለም፡፡ ኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት የአደጋው ከባድ ተጠቂ ስትሆን 24 ሰዎችና ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጉ እንስሳት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን