አሜሪካ በ10 የምያንማር ወታደራዊ መሪዎችና አካላት ላይ ማእቀብ ጣለች
ጆ ባይደን የምያንማር ወታደር በአሜሪካ ያለውን 1ቢሊዮን ዶላር አንዳያንቀሳቅስ እርምጃ ወስደዋል
የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ከምያንማር ወታደር ጋር ግንኙነት ያላቸው 10 በሚሆኑ የአሁንና የቀድሞ ባለስልጣናት ላይ ማእቀብ መጣሉን አስታውቋል
አሜሪካ መፈንቅለ መንግስት ባካሄዱት የምያንማር ወታደራዊ መሪዎችና አካላት ላይ ተከታታይ ማእቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ10 የሚሆኑ የአሁንና የቀድሞ ባለስልጣናትና ከምያንማር ወታደራዊ ወይም የጸጥታ ሃይል ጋር የተገናኙ ሶስት አካላትን በጥቁር መዝገብ ውስጥ መስፈራቸውን ገልጿል፡፡ በኋይት ሀውስ በወጣው መረጃ መሰረት፣ የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴርም ወሳኝ የሚባሉ እቃዎች ለምያንማር ወታደርና ሌሎች አካላት እንዳይደርሱ አግዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካው ዩኤስአይዲ የምያንማር መንግስት ግብረሰናይ ተቋማትንና የግል ተቋማትን ሊደግፍ የሚችልበትን 42.4 ሚሊዮን ዶላር ማገዱ ተዘግቧል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ረብዕ እንዳስታወቁት አስተዳደራቸው በአሜሪካ የሚገኘውን የመንግስት 1 ቢሊዮን ዶላር የምያንማር ጄነራሎች እንዳያገኙ ርምጃ መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡ ባይደን የምያንማር ወታደር ፕሬዘዳንት ኡ ዊን ሚይንትና መሪዋን ሳን ሱ ቺን ጨምሮ የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲለቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደር በፈረንጆቹ 2020 የተካሄደውና የናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ ሁለቱንም ምክርቤቶች በአብለጫ ድምጽ ያሸነፈበት ምርጫ የተጭበረበረ ነው በማለት የምክር ቤቱ ስብሰባዎች እንዲራዘሙ ይፈልጋል፡፡ በዚህም ምክንያት ጦሩ መፈንቅለ መንግስት አድርጓል፡፡
የምያንማር ምርጫ ኮሚሽን ግን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡
በሀገሪቱ መፈንቅለ መንግስቱን ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ እንድ ሰው የተገደለ ሲሆን ሌሎች ስድስት ሰልፈኞች ቆስለው በመታከም ላይ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታት በሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን የኃይል እርምጃ አውግዟል፡፡