የአረብ ሊግ በሊቢያ ጉዳይ የውጭ ኃይሎች እንዳይገቡ አስጠነቀቀ
በግብፅ ጠሪነት የአረብ ሊግ ከፍተኛው አካል በትናንትናው እለት በካይሮ ባደረገው ስብሰባ የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ግጭቱ የውጭ ተዋጊዎችን ስምሪት ወደሚጠይቅበት ደረጃ እንዳያደርሱት አስጠንቅቋል፡፡
በሀገሪቱ የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ የሚገቡ አካላትም ድርጊታቸው ተቀባይነት እንደይሞረው ሊጉ አስታዉቋል፡፡
የውጭ ጣልቃ ገብነት የውጭ ጽንፈኞች እንዲገቡ ያደርጋል በማለት ነው ሊጉ ያስጠነቀቀዉ፡፡
አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለሊቢያና ጎረቤቶቿ ብሎም ለቀጣናው ትልቅ ስጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በጦር መሳሪያ የታገዘ ውጊያ እንዲቆምና ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት ብቸኛው መፍትሄ ፖለቲካዊ ንግግር መሆኑንም በስብሰባአው ላይ ተወያይተዋል፡፡
በአካባቢው ሰላምን ለመመለስና የሽብር ቡድኖች እንዳይገቡ ለማድርግ ሁሉም ፖለቲካው ንግግርን እንዲመርጥ የአረብ ሊግ አሳስቧል፡፡