አውስትራሊያ በተከሰተው የሰደድ እሳት ሳቢያ በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ታወጀ
በአውስትራሊያ ኒው ሳውዝ ዌልስ በተከሰተው ሰደድ እሳት ሳቢያ አስቸኳይ ጊዝ አዋጅ የታወጀ ሲሆን በሀገሪቱም ከፍተኛ የሙቀት መጠን መመዝገቡ ተገለጿል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ በአውስትራሊያ ክብረ ወሰን የሆነ ሙቀት ተመዘግቦ ነበር፡፡ ይሁንና ትናንትና የተከሰተው ሙቀት ደግሞ ከማክሰኞው መብለጡንና 41 ነጥብ 9 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መሆኑን ቢቢሲ ዘገቧል፡፡
በአገሪቱ ኒው ሳውዝ ዌልስ የተከሰተው ሰደድ እሳትም ምክንያቱ በአገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ይህንን ተከትሎም የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ግላዲስ ብርጂክላና የሰባት ቀናት አስቸካይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውቀዋል፡፡
በግዛቲቱ የታወጀው አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ለአካባው አስተዳዳሪዎች ተጨማሪ አቅም ይሰጣቸዋል ነው የተባለው
ሰደድ እሳት በአውስትራሊያ ለወራት የዘለቀ ችግር መሆኑ ተገለጿል፡፡
በዚህም ስድስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን በመቶዎች ሚቆጠሩ ቤቶች ወድመዋል ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ባለፈም በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ማሳ መቃጠሉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም በጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ላይ ተቃውሞ ተነስቶባቸዋል፡፡
ይህ ሰደድ እሳት ተከስቶ ሳለ እርሳቸው ከቤተሰባቸው ጋር ሃዋይ መሆናቸው የተቃውሞው መነሻ ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ