ቡርኪናፋሶ የሁለት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች
በቡርኪናፋሶ ፅንፈኛ ታጣቂዎች ትናንት ታህሳስ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በፈጸሙት ጥቃት 35 ንፁሀን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 31 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡
ለጥቃቱ አፀፋዊ ምላሽ በመስጠት ላይ የነበሩ 7 ወታደሮችና ከታጣቂዎቹም 80 የሚጠጉ መገደላቸው ተነግሯል፡፡
እስካሁን ለጥቃቱ ሀላፊነት ወስዳለሁ ያለ አካል አልተገኘም፡፡
በወሩ መጀመሪያ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች በቤተ አምልኮ በከፈቱት ተኩስ 14 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡
በሀገሪቱ ከ2015 ወዲህ የሽብር ጥቃቶች ተጠናክረዋል አንፃራዊ ሰላም የነበራት ቡርኪናፋሶ በጎረቤት ሀገር ማሊ ከመሸጉ ታጣቂዎች ጋር በተያያዘ የሽብር ጥቃት ሰለባ እየሆነች መጥታለችም ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ክሪስቲያን ካቦሬ ለጠፋው የንፁሃን ህይወት የሁለት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን አውጀዋል፡፡