ቻይናን ጨምሮ 20 ሀገራት እስካሁን በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡
ጣሊያን 7,000 ሰዎችን አሳፍሮ ከቻይና ወደ ዳርቻዋ በደረሰ መርከብ ውስጥ 2 የቫይረሱ ተጠቂዎች በመገኘታቸው ተሳፋሪዎቹ በመርከቡ እንዲቆዩ አድርጋለች፡፡ ሩሲያ ከቻይና ጋር በሩቅ ምስራቅ የሚያዋስናትን ድንበር ዘግታለች፡፡ በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና እና ከቻይና ውጭ የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል፡፡ ቻይና በሀገሯ የሚካሄዱ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ሁሉ እንዲራዘሙ ወስናለቸች፡፡ የቫይረሱ መነሻ የሌሊት ወፎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመራማሪዎች ገልጸዋል፡፡