ዝቅተኛ የነፍስወከፍ ገቢ ካላቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው
የነፍስወከፍ ገቢ አንዱ የእድገት መጠን መጠን ነው።
የዜጎች የነፍስወከፍ ገቢ መጠን ሀገራት ያሉበትን የኢኮኖሚ ደረጃ ለመለካት የሚያስችል አንዱ መስፈርት ነው።
በአደጉ ሀገራት ያሉ ዜጎች የተሻለ የነፍስወከፍ ገቢ ይኖራቸዋል። በደሃ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች የነፍስወከፍ ገቢ ደግሞ ዝቅተኛ እንደሚሆን እሙን ነው።
ዝቅተኛ የነፍስወከፍ ገቢ ካላቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
ቡሩንዲ በ249.22 ዶላር እለታዊ የነፍስወከፍ ገቢ ካላቸው ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች።