ድጋፉ አጋርነት እና ማስታወስን ለማሳየት በማሰብ የተደረገ ነው
ኮሞሮስ “ብዙ ባይፈይድም” ያለችውን 100 ዩሮ ለቻይና ሰጠች
“ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም” እንዲሉ አበው ኮሞሮስ በመሰረተችው ትብብር በኩል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተፈተነች ያለችውን ቻይናን ሊደግፍ ይችላል በሚል የ100 ዩሮ ድጋፍ ማድረጓን ጅቡቲ ፕሬስ አስነብቧል፡፡
ድጋፉ የተወሰነ ካርቶን የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ጭምብል) ይገዛ እንደሆነ እንጂ ብዙ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ እናውቃለን ያሉት የትብብሩ ፕሬዝዳንት ’የቻይናን ብቃት እናውቃለን ሆኖም ያለንን አጋርነት ለማሳየት እና ከጎኗ መሆናችንን ለማሳወቅ‘ ስንል ይህችን ትንሽ ገንዘብ ለመስጠት ወደናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ቻይና ከኮሞሮስ ጋር የቀረበ ወዳጅነት አላት፡፡ ኮሞሮስ እ.ኤ.አ በ1975 ላገኘችው ነጻነትም ቻይና ነበረች ቀድማ እውቅናን የሰጠችው፡፡ይህ ግንኙነታቸው ይበልጥ ከቅርብ አመታት ወዲህ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡