የእሳቱ የእስካሁን ጉዳት እና አሁን ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል?
ባለፈው መስከረም ወር የጀመረው የአውስትራሊያ የጫካ ሰደድ እሳት እስካሁን በርካታ ጥፋቶችን አስከትሏል፡፡ለሰደድ እሳቱ መከሰት ዋነኛ ምክኒያት በሀገሪቱ ያለው ከፍተኛ ሙቀት እና ለወራት የዘለቀ ድርቅ ቢሆንም ሆን ብለው እሳት በመለኮስ እና ችግሩ እንዲባባስ በማድረግ የተጠረጠሩ 24 ሰዎች ተይዘዋል፡፡
ዋነኛ ተጠቂ በሆኑት ኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ ግዛቶች ላይ የሚገኙ እሳቶች ገጥመው ከባድ ቃጠሎ ሊከሰት እንደሚችል ተሰግቷል፡፡