በጉዞ ላይ ሳሉ በኮሮና የሚያዙ ደንበኞቹን የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የኤሚሬትስ አየር መንገድ አስታወቀ
የሚታመሙ መንገደኞች እስከ 150 ሺ ዩሮ ድረስ ወጪያቸው እንዲሸፈን ለመጠየቅ ይችላሉም ተብሏል
በአየር መንገዱ መዳረሻ ስፍራዎች ተለይተው የሚቆዩ ደንበኞቹን ወጪ እንደሚሸፍንም ገልጿል
በጉዞ ላይ ሳሉ በኮሮና የሚያዙ ደንበኞቹን የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የኤሚሬትስ አየር መንገድ አስታወቀ
በአየር መንገዱ በመጓዝ ላይ ሳሉ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ደንበኞቹን የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የኤሚሬትስ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡
ወጪው ያለምንም የጉዞ ደረጃ ልዩነት በነጻ እንደሚሸፈን ያስታወቀው አየር መንገዱ መንገደኞቹ በአየር መንገዱ መዳረሻ ስፍራዎች ተለይተው ሊቆዩ የሚችሉበትን ወጪ እንደሚሸፍንም ገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ይህን የሚያደርገው ደንበኞቹ በልበ ሙሉነት ለጤንነታቸው ዋስትና አግኝተው ሊጓዙ የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማሰብ ነው፡፡
ለዚህም ከምክትል ፕሬዝዳንት፣ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ከሼክ ሞሃመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም አቅጣጫ ተሰጥቶታል፡፡
ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም ሆነ ከሌሎች ሃገራት በአየር መንገዱ በመጓዝ ላይ ሳሉ በቫይረሱ ተይዘው የሚታመሙ መንገደኞች እስከ 150 ሺ ዩሮ ድረስ ወጪያቸው እንዲሸፈን ለመጠየቅ ይችላሉም ተብሏል፡፡
ተገልለው ለሚቆዩባቸው 14 ቀናትም በቀን 100 ዩሮ ይከፈልላቸዋል፡፡
እንደ ኤመራቲ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ግን ይህ የሚቆየው እ.ኤ.አ እስከ ጥቅምት 30 2020 ድረስ ብቻ ነው፡፡