የአውሮፓ ህብረት አባሉን ጣሊያንን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ይቅርታ ጠየቀ
የአውሮፓ ህብረት አባሉን ጣሊያንን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ይቅርታ ጠየቀ
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ እየተጠቃች ያለችው ጣሊያን ቫይረሱን ለመከላከል እያደረገች ያለውን ጥረት ህብረቱ አለመደገፉን ተከትሎ ነው የብራሰልሱ ተቋም ሮምን ይቅርታ ለመጠየቅ የተገደደው፡፡
የህብረቱ ኮሚሽን ለጣሊያ መድረስ ባለብኝ መልኩ አልደረስኩላትም ብሏል፡፡ይሁንና ህብረቱ አሁን ቫይረሱ ያመጣውን ቀውስ ሃገሪቱ የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍም ይፋ አድርገዋል፡፡
በጣሊያን ሀገር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በርካቶችን ለህልፈት ህይወት ብዙዎችን ደግሞ ለጉዳት እየዳረገ ሳለ የአውሮፓ ህብረት ዝምታ ከፍተኛ ጥያቄ ሆኖ መቆየቱም ተዘግቧል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡረሱላ ቮን ድረ ለይን ብዙ የህብረቱ አባል ሀገራት ከመጀመሪያው ጀምሮ በራሳቸው ችግር ላይ ተጠምደው እንደነበር፣ በጣሊያ ላ ሬፐብሊካ ጋዜጣ ላይ የወጣው ጹህፍ ያመለክታል ተብሏል፡፡
የጣሊያኑ ሊግ ፓርቲ በጣሊያን የአውሮፓ ህብረት አባልነት ደስተኛ አለመሆኑን የገለጸ ሲሆን የህብረቱ ደጋፊዎችም ህብረቱ ለጣሊያን ችግር አልደረሰላትም እያሉ ነው፡፡በሃገሪቱ እስካሁን 12 ሺ 915 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 115 ሺ 242 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ አለባቸው ተብሏል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡረሱላ ቮን ድረ ለይን "ይህንን ወረርሽኝ በጋራ መከላከል እንደምንችል ማሳየት ነበረብን፣ ይህንን ማድረግ አለመቻላችን መወገዝ አለበት ብለዋል፡፡
“አሁን አውሮፓ ከጣሊያን ጋር ይተባበራል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስና ኦስትሪያ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጎዱት መካከል እንደ ጣሊያን ቦንድ መግዛትና ማገዝን ተቃውመው ነበር ተብሏል፡፡
የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ "ጠንካራና ፈጣን የጋራ የሆነ፣ እንዲሁም የተቀናጀ የአውሮፓ ምላሽብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡ የዘገየ ምላሽ ግን ጥቅም የለውም "
እስካሁን በጣሊያን በቫይረሱ 14ሺ የሚደርሱ ሰዎች ሞተዋል፡፡