የ10ሩ የአለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች አጠቃላይ አመታዊ ገቢ 1.3 ቢሊየን ዶላር ደርሷል
የስፖርቱ አለም በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ኢንዱስትሪ ነው።
ስፖርተኞች በሙያቸው ከሚከፈላቸው ገንዘብ በተጨማሪ በማስታወቂያ እና ስፖንሰር ስምምነት ሚሊየን ዶላሮችን ያገኛሉ፡፡
ፎርብስ በ2024 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች በሚል ባወጣው ዝርዝር ፖርቹጋላዊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን በቀዳሚነት አስቀምጦታል፡፡ ሮናልዶ በ12 ወራት ውስጥ ከአልናስር ጋር ባለው ኮንትራት 200 ሚልየን ዶላር ሲከፈለው ከኳስ ሜዳ ውጭ ደግሞ 60 ሚሊየን ዶላር አግኝቷል፡፡
የጎልፍ ተጨዋቹ ጆን ራሀም በ218 ሚሊየን ዶላር ባለፉት አራት አመታት እየመራ ያለውን ሮናልዶ ይከተላል። የኢንተር ሚያሚው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ135 ሚሊየን ዶላር ገቢ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡
10 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች አጠቃላይ አመታዊ ገቢ 1.3 ቢልየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ 10ሩ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ስፖርተኞች ገቢ 100 ሚልየን እና ከዛ በላይ ሆኗል፡፡
በደረጃ ውስጥ ከተካተቱ የስፖርት አይነቶች መካከል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ብዙውን ቁጥር ሲሸፍኑ ቅርጫት ኳስ በሁለተኛነት ይከተላል፡፡
በ2024 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኞች እና አመታዊ ገቢያቸውን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦