ስፖርት
በ2022/23 ከፍተኛ ገቢ ያስገቡ 10 ክለቦች
ሪያል ማድሪድ ክብረወሰን የሆነ የ831 ሚሊየን ዩሮ ገቢ በማስገባት ከ2017/18 በኋላ ከሲቲ ደረጃውን ቀምቷል
ከፍተኛ ገቢ ያስገቡት 20 ክለቦች 10 ነጥብ 5 ቢሊየን ዩሮ ገቢ ማግኘታቸው ተገልጿል
ሪያል ማድሪድ ከ2017/18 በኋላ ከእግርኳስ ከፍተኛውን ገቢ ያስገባ የአለማችን ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።
ደሎይት የተሰኘው ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የስፔኑ ክለብ በ2022/23 የውድድር አመት ክብረወሰን የሆነ የ831 ሚሊየን ዩሮ ገቢ አስገብቷል።
በውድድር አመቱ የሻምፒዮንስ ሊግ፣ ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ ያሳካው የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ 826 ሚሊየን ዩሮ በማስገባት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ከፍተኛ ገቢ ያስገቡት 20 ክለቦች ገቢ ካለፈው የውድድር አመት በ14 በመቶ አድጎ 10 ነጥብ 5 ቢሊየን ዩሮ መድረሱም ነው የተገለጸው።
ሌስተር ሲቲ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ኤቨርተን ከምርጥ 20 ዝርዝሩ ውጭ ሆነዋል።
በአለማችን ከፍተኛ ገቢ በሚያስገቡ 20 የእግርኳስ ክለቦች ዝርዝር ውስጥ ባለፉት ሁለት አመታት በጥቂቱ 10 ክለቦችን ያስመዘገበው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ በ2022/23 የውድድር አመት ስምንት ክለቦችን ብቻ አስመዝግቧል።
ኒውካስትል በ287 ሚሊየን ዩሮ፤ ዌስትሃም ደግሞ በ275 ሚሊየን ዩሮ 17ኛ እና 18ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በ2022/23 የውድድር አመት ከፍተኛ ገቢ ያስገቡ 10 ክለቦችንን ይመልከቱ፦