ምዋንጊ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ አመጽ ኬንያውያን ሲሰቃዩ ሲያይ የመብት ተሟጋች እንዲሆን አጋጣሚ ሆኖለታል
ምዋንጊ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ አመጽ ኬንያውያን ሲሰቃዩ ሲያይ የመብት ተሟጋች እንዲሆን አጋጣሚ ሆኖለታል
የኬንያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቦኒፌስ ምዋንጊ የፈረኝጆቹ 2020ን የላቀ ወጣት ሰላም አስፋኝ ሽልማትን በስቸንገን የሰላም ፋውንዴሽንና በአለም የሰላም ፎረም ተቀብሏል፡፡
የለክሰንበርግ የሰላም ሽልማት ከአለም ውድ ከሚባሉ ሽልማቶች መካከል የሚጠቀስ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፋውንዴሽኑ ምዋንጊ ለማህበራዊ ለውጥና ፍትህ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ከወጣቶች መካከል እንዲመረጥ አስችታል ብሏል፡፡
ድርጀቱ እንደገለጸው ምዋንጊ ለፎቶግራፍ ባላቸው ፍቅር ከሚታወቁ ኬንያውያን ወጣቶች አንዱ ነው፤ምዋንጊ የፎቶግራፍ ስራው ላይ እያለ ኬንያውያን በፈረንጀች 2008 ምርጫን ተከትሎ በመጣው አመጽ ወቅት ሲሰቃዩ ሲያይ የመብት ተሟጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ምዋንጊ በተከታታይ የፎቶግራፍ ስራዎቹም አለምአቀፍ ሽልማቶችን አሸፏል፤ በብጥብጡ ወቅት ያነሳቸውን ሮቶዎች ሀገርአቀፍ አውደርእይ በማዘጋጀት ኬንያውያን ካለፈ ታሪካቸው እንዲማሩ ለማድረግ ሞክሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ምዋንጊ ፓዋ254 የሚል ክበብ በመመስረት ፕሮግራም ከማዘጋጀት በተጨማሪ ለተለያዩ የወጣት ድርጅቶች የመሰብሰቢያ ቦታ ሆኖ እንዲያገለግል አድርጓል፡፡
የወጣቱ ፍትህን ለማስፈንና ሙስናን ለመዋጋት ያደረገው ብርታትና ቆራጥ አቋም በድርጂቱ የሚደነቁ የምዋንጊ ባህሪያት ሆነው እንዲሸለም አስችለውታል፡፡
የለክሰንበርግ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 2012 በስቸንገን የሰላም ፋውንዴሽን የተቋቋመ ሲሆን አላማውም በአም ዙሪያ ለሰላም ላቅ ያለ አበርክቶ ያላቸውም ሰዎች መሸለም ነው፡፡
በየአመቱ በተለያዩ ዘርፎች ከሰላም ተሟጋች እስካ የአካባቢ ተሟጋች ሽልማቶች ይሰጣሉ፡፡