የማሪየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት በጥቁር አሜሪካዊቷ ጥያቄ መነሻነት የዘረኝነትን ትርጉም ሊቀይር መሆኑን ገለጸ
የማሪየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት በጥቁር አሜሪካዊቷ ጥያቄ መነሻነት የዘረኝነትን ትርጉም ሊቀይር መሆኑን ገለጸ
የ 22 ዓመቷ የዳርኬ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ጥቁር አሜሪካዊ ተማሪ ለማሪየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት አዘጋጆች የዘረኝነት ትርጉም እንዲቀየር ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ማቅረቧ ተሰምቷል፡፡ኬኔዲ ሚትቹም የተባለችው ይህች ተማሪ ለመዝገበ ቃላት አዘጋጆቹ ተደጋጋሚ የኢሜል መልዕክቶች መላኳ የተገለጸ ሲሆን አዘጋጆቹም ለጥያቄዋ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ዘረኝነት ሰው በቆዳ ቀለም የማግለል ብቻ እንደሆነ ተደርጎ እየተተረጎመ ያለበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን የገለጸችው ሚትቹም በቆዳ ቀለም ላይ ተመስርቶ የመፈረጅ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊና ተቋማዊ በሆነ መልኩ የሚፈጸም ነው ብላለች፡፡
በአጠቃላይ ዘረኝነት በቆዳ ቀለም ምክንያት የበላይ የመሆንና የመጠቀም ሥርዓት መሆኑን ገልጻለች፡፡በቆዳ ቀለም ብቻ ማግለል ዘረኝነትን እንደማይገልው ለመዝገበ ቃላት አዘጋጆቹ የተናረችው ተማሪዋ ዘረኝነት ይህ ብቻ ሳይሆን ከኋላ ተቋማዊ አቅም ያለው መሆኑን ገልጻለች፡፡
አሁን ላይ ያለው የዘረኝነት ትርጉም በቆዳ ቀለም ማግለልንና የበላይነትን ማሳየት ሲሆን ይህም በፖለቲካዊና ማህበራዊ ስርዓቶች ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ዘር ችሎታንና አቅምን ይወስናል ብሎ የማሰብ አባዜ እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ይህንን ትርጉም የሰጡት የሶሺዮሎጅ ምሁሩ ፓትሪሲያ ቢዶል መሆናቸው ተገልጿል፡፡የመዝገበ ቃላቱ አርታኢዎች ታዲያ ይህ ነገር ማሻሻያ እንዳልተደረገለት አንስተው አሁን ማሻሻያ እንደሚደረግና ቃላትን ማስተካከል እንደሚጠይቅ አስታውቀዋል፡፡
አዘጋጆቹ እንዳሉት ዘረኝነት ትርጉም በደንብ ግልጽ እንደሚደረግ የገለጹ ሲሆን ይህንን ውሳኔ እንዲወስኑ ያደረገቻቸውን ተማሪ አመስግነዋል፡፡ ጉዳዩ ተባብሶ የመጣው ደግሞ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ነው፡፡የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በአሜሪካ የሳምንታት የፈጀ የጸረ-ዘረኝነት ተቃውሞ ማስነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡
ተማሪዋ አዘጋጆቹ ለጥያቄዋ ምላሽ በመስጠታቸው መደሰቷን ለሲኤንኤን ገልጻለች፡፡