ኖርዌይ፣አየርላንድ እና ስፔን ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ አስታወቁ
ለፍስጤም የሀገርነት እውቅና በመሰጠት ጉዳይ የአውሮፓ ሀገራት ወደ ሁለት ጎራ ተከፍለዋል
ለፍስጤም የሀገርነት እውቅና በመሰጠት ጉዳይ የአውሮፓ ሀገራት ወደ ሁለት ጎራ ተከፍለዋል
ኖርዌይ፣ ከእስራኤል ጋር ሰላም ይፈጥራል በሚል ተስፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጆኔስ ጋህር ስቶሬ በዛሬው እለት ተናግረዋል።
አየርላንድ እና ስፔንም ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ "የቱ ስቴት ሶሉሽንን" በመፍትሄነት የሚቀበሉት የአውሮፓ ህብረት አባላቱ እውቅና የመስጠት ሀሳብ እንዳላቸው አመላክተዋል።
የሶስቱ ሀገራት ውሳኔ ፍልስጤም ከአጠቃላይ 193 የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት በ143ቱ የሀገርነት እውቅና ማገኝቷን የሚያረጋግጥላት ነው፡፡
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስተር ጆናስ ጋርስቶር መንግስታቸው ለፍልሰጤም ሙሉ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት መወሰኑን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚንስተሩ ‘’በጋዛ እየሆነውን ለማስቆም እስራኤል እና ፍልስጤም ሁለት የተለያዩ ሀገራት መሆናቸውን መቀበል አስፈላጊ ነው ይህን ለማረጋገገጥ ደግሞ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መሰጠት ግድ ነው’’ ብለዋል፡፡
በጋዛ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀንን የቀጠፈው ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ሌሎች ሀገራትም የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተሉ ጠይቀዋል፡፡
እውቅናው ከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ተግበራዊ የሚደረግ ሲሆን ኖርዌይ ከፍልስጤም ጋር የሚኖራት ግንኙነትን የሚወስኑ ጉዳዮች በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
አየርላንድ ኖርዌን በመከትል እውቅና ስትሰጥ ስፔን ተያዘው ወር ከመጠናቀቁ በፊት ተመሳሳዩን አደርጋለሁ ብላለች ፡፡
ፖርቹጋል፣ ቤልጅየም፣ ስሎቫኒያ እና ማልታ በጉዳዩ ላይ እያጤኑበት መሆኑ ታውቋል፡፡
ከ35ሺህ በላይ ንጹሀንን የቀጠፈው የጋዛ ጦርነት ምእራቡ አለም በፍልስጤም ላይ ያለውን አተያይ እንዲቀይር ያደረገው ይመስላል፡፡
"ቱ ስቴት ሶልዩሽን" በመባል የሚጠራው በዋናነት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቀና መሰጠት ላይ በሚያጠነጥነው እና የእስራኤልንም ገለልተኛ ሀገርነት በሚወስነው ምክረ ሀሳብ ላይ የቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደደር ከፍተኛ ተቃውሞ አለው፡፡
ቴልአቪቭ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ማለት ሀማስ እንዲፈረጥም መፍቀድ ማለት ነው ትላለች፡፡
የአውሮፓ ለሁለት መከፈል
አውሮፓ በጉዳዩ ላይ ለሁለት ተከፍሏል። ስፔን ፔልጅየም እና ፖርቹጋልን መሳሰሉ ሀገራት ፍልስጤም በተከለለ ድንበር አራሷን ችላ ሀገር ሆና መቆሟ እስራኤል ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመሳደር እና የዛን ቀጠና ውጥንቅጥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ለመቋጨት መፍትሄ ነው ብለው ያምናሉ፡፡
በአንጻሩ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያን የመሳሰሉ ሀገራት በጉዳዩ ላይ የተለሳለሰ አቋም የሚያንጸባርቁ ገሚሶችም ከእስራኤል ጋር ባላቸው ወዳጅነት ከነአካቴው የፍልስጤምን ሀገር መሆን የማይቀበሉ ናቸው፡፡
የምእራቡን አለም እና የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናን በተለያየ አቋም ልዩነት የከፋፈለው የፍልስጤም ሀገር የመሆን ነገር ከጀርባው ትልቅ ታሪካዊ እና ጂኦፖለቲክሳዊ ዳራ የተሸከመ ነው