ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ለፈረንሳይ እንደነውር መታየቱ ማብቃቱን ፕሬዝደንት ማክሮን ተናገሩ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከጆርዳን በስተምዕራብ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አሳልፈው እንደማይሰጡ በመግለጽ የፍልስጤምን ሉአላዊነት ተቃውመዋል።
ማክሮን ፓሪስ የ'ቱ ስቴት ሶሉሼን' ተግባራዊ እንዳይደረግ እስራኤል ከተቃወመች ልትወስን እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል
ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ለፈረንሳይ እንደነውር መታየቱ ማብቃቱን ፕሬዘዳንት ማክሮን ተናገሩ።
ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መሰጠት ለፈረንሳይ ነውር መሆኑ አብቅቷል ያሉት ማክሮን ፓሪስ የ'ቱ ስቴት ሶሉሼን' ተግባራዊ እንዳይደረግ እስራኤል ከተቃወመች ልትወስን እንደምትችል ፍንጭ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፈረንሳይ የምትሰጠው የተናጠል እውቅና መሬት ላይ ያለውን እውነት የሚቀይረው ባይሆንም፣ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከጆርዳን በስተምዕራብ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አሳልፈው እንደማይሰጡ በመግለጽ የፍልስጤምን ሉአላዊነት ተቃውመዋል።
በፈረንጆች 2014 የፈረንሳይ ህግ አውጭዎች መንግስታቸው ለፍልስጤም እውቅና እንዲሰጥ በማሳሰብ በፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ አቋም ላይ ትንሽ ተጽዕኖ ማድረግ ችለው ነበር።
ይህ የማክሮን አስተያየት በባለፈው የፈረንጆቹ አመት ጥር ወር የተቀሰቀሰውን የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ተከትሎ በጋዛ እየተፈጸመ ያለው የፍልስጤማውያን ግድያ የምዕራባውያን መሪዎችን ትግስት እየተፈታተነ መሆኑን የሚያመላክት ነው ተብሏል።
"በቀጣናው ካሉ አጋሮቻችን በተለይም ከጆርዳን ጋር እየሰራንበት ነው። በአውሮፖ እና በጸጥታው ምክርቤት አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ነን። የፍልስጤም ሀገርነት እውቅና የፈረንሳይ ነውር አይደለም" ሲሉ ከጆርዳኑ ንጉስ አብዱላህ ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ማክሮን "ለረጅም ጊዜ ህልማቸው የተጨናገፈባቸው ፍልስጤማውያን እዳ አለብን። በክፍለ ዘመኑ በእስራኤላውያን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ ያሳስበናል። ቀጠናው ከትርምስ ናፋቂዎች ነጻ እንዲሆን እንሰራለን" ብለዋል።
የማክሮን አስተያየት በእስራኤል ላይ ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር ነው ተብሏል።
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ባለው መጠነ ሰፊ የመሬት እና የአየር ጥቃት እስካሁን የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 28ሺ ደርሷል።
አብዛኞቹ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ለፍለስጤም የሀገርነት እውቅና ቢሰጡም፣ አብዛኞቹ ምዕራባውያን ሀገራት ነጻ ፍልስጤም የምትፈጠረው ከእስራኤል ጋር በሚደረግ ስምምነት ነው በሚል ምክንያት እውቅና ነፍገዋታል።
ማክሮን የእስራኤልን ራፋን የማጥቃት እቅድ ከባድ የሰብአዊ ቀውስ ያስከትላል ሲሉ ተችቸውታል።