በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ በግጭቱ ከሞቱት መካከል አራቱ የፖሊስ አባላት ናቸው
በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ በግጭቱ ከሞቱት መካከል አራቱ የፖሊስ አባላት ናቸው
በወረዳው 022 ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮሬብ በተባለ ቦታ በግለሰቦች ጸብ በተፈጠረው ግጭት 3 የአካባቢውን ነዋሪዎች ጨምሮ 4 የፖሊስ አባላት መሞታቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡
ለግጭቱ መነሻ የሆኑ ሌሎች ምክንያቶች በመጣራት ላይ መሆናቸውንም ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡ አካባቢውን ለማረጋጋት የፀጥታ ሃይሉና አመራሩ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛልም ብሏል፡፡
ጽ/ቤቱ ዛሬ ባወጣው መረጃ በተፈጠረው ግጭት ህይወታቸው ያለፈው የፖሊስ አባላት አስከሬን የአማራ ልዩ ሃይል ፣ የወረዳው ፖሊስ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በልዩ ልዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴወች ታጅቦ ወደ ትውልድ ቦታቸው ሽኝት እንደተረገለት ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡