ፕሬዘዳንት ኪር 30 እስረኞችን በመፍታት ለእርቅ ምልክት አሳዩ
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር የፖለቲካ አክቲቪስቱን ፒተር ቢያርንና ባለሀብት ካርቢና ዎልጎክን ጨምሮ 30 እስረኞችን በመፍታት ሰላምና እርቅ ለማምጣት መልካም ምልክት ማሳየታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ በፕሬዘዳንት ኪርና በተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቸር መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ሊተገበር አልቻለም፤ ስለሆነም የፕሬዘዳንቱ እስረኞች የመፍታት ዉሳኔ ለእርቅና ለሰላም ያላቸውን ተነሳሽነት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
የእስረኞቹ መፈታት ይፋ የሆነው ባለፈው ሀሙስ እለት ለነበር፡፡
የመፍታት ዉሳኔው የተላለፈው ፕሬዘዳንት ኪር የገናንና የአዲስ አመት በአልን ምክንያት በማድረግ የጁባን ማእከላዊ እስርቤት ከጎበኙ በኋላ ሲሆን፣ሌሎች እስረኞችም እንደሚፈቱ ፕሬዘዳነንቱ ገልጸዋል፡፡
ከተፈቱት መካከል የሀገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል ተብለው የተከሰሱት ታዋቂው የፖለቲካ አክቲቪስት ፒተር ቢያርና በበጎአድራጎት የሚታወቀው ባለሀብት ካርቢና ዎልጎክ ይገኙበታል፡፡
ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2011 ከሱዳን ከተገነጠለች በኋላ ብዙም ሳትቆይ በሁለት ጎራ በተሰለፉ ልጆቿ የማያባራ የእርስበእርስ ጦርነት ውስጥ ገብታ በ10 ሺህ የሚቆመሩ ዜጎቿ ለሞት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል፡፡
በአንድ በኩል በፕሬዘዳንት ኪር በተቃራኒ ወገን ሪክ ማቸር በመሆን ጦርነት ሲያካሄዱ ቆይተዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2018 ለአምስት አመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም በአዲስ አበባ ስምምነት ቢፈርሙም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም፡፡