ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ብሪታኒያ በስምምነቱ አትራፊ ናት ብለዋል
የአውሮፓ ሕብረትና ብሪታኒያ ከፍች (ብሬግዚት) በኋላ በሚኖራቸው የንግድ ግንኙነት ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን ሕብረቱ አስታወቁ፡፡
የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ለየን ብራሰልስ እና ለንደን በረጅምና ሰፊ የድርድር መንገድ ቢያልፉም ለሁለቱ ወገኖች ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ከሆነ የንግድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ብለዋል፡፡
በቢቢሲ በቀጥታ ሥርጭት በተላለፈው መግለጫቸው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሉዓላዊነት ማለት በጋራ መስራት፣መማር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፈታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በጋራ መፍታትና ወደ ከፍታ መጓዝ ቢዚህ ዘመን አስፈላጊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ ይህም በቀጣይ በሁሉም የሕብረቱ አባል ሀገራት መካከል የሚኖር ነው ብለዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት ተደራዳሪዎች ሚዛናዊ የሆነ ድርድር በማድረጋቸው ከፍተኛ ምስጋና አለኝ ያሉት ፕሬዚዳንቷ በቀጣይ ከብሪታኒያ ጋር በሚኖረው የንግድ ግንኑነት ሁለታችንም ተጠቃሚዎች ነን ሲሉ ተናግረዋል በመግለጫቸው፡፡
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በበኩላቸው ሃገራቸው በስምምነቱ አሸናፊ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ይህ ለብሪታኒያውያን የፖለቲካ ድል ነው ያሉት ቦሪስ በብዙ ዘርፎች ለንደን ትርፋማ እንደሆነች ጠቅሰዋል፡፡
ሕብረቱ ከብሪታኒያ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት የሚመለከተውን ግብረ ኃይል የሚመሩት ፈረንሳዊው ዲፕሎማት ሚሼል በርናንድ የሕብረቱ ጥንካሬ አንድነቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እርሳቸውም የሕብረቱ ባልደረባ በመሆናቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል፡፡
አውሮፓ ሕብረት ፕሬዚዳንትና የግብረ ኃይሉ መሪ ሚሼል በርናንድ በመግለጫቸው የአውሮፓ ሕብረት የሚታወቅበትን የአንድነትና የጥንካሬ እሴቱን ይዞ እንደሚቆይ አስታውቀዋል፡፡