ቱርክ በፕሮፓጋንዳ ክስ 16 የኩርድ ጋዜጠኞችን አሰረች
ቱርክ ባለፋት አስርት አመታት በርካታ ጋዜጠኞችን ማሰሯ ተገልጿል
ጋዜጠኞቹ ክስ ሳይመሠረትባቸው ከታሰሩ ሁለት ሳምንታት አስቆጥረዋል
በቱርክ ፍርድ ቤት የሽብር ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተዋል በሚል ባለፈው ሳምንትበቁጥጥር ስር የዋሉ 16 የኩርድ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች ፍርድ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የመገናኛ ብዙሃን እናየህግ ጥናት ማህበር እና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ሃሙስ እለት አስታወቁ።
በደቡብ ምስራቅ ዲያርባኪር ከተማ መደበኛ ክስ ሳይመሰረትባቸው ለስምንት ቀናት በእስር ላይ መቆየታቸውን፣ አቃቤ ህግ ሁለት ጊዜ እንዲራዘም መጠየቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ እንደገለጸው ቱርክ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከሌሎች ሀገራት በበለጠ ብዙ ጋዜጠኞችን ታስራለች እና በርካታ የሚዲያ ቡድኖች ያለፈውን ሳምንት እስራት “ጨካኝ” ሲሉ አውግዘዋል።
ከታሰሩት መካከል የዲክሌ ፊራት ጋዜጠኞች ማህበር ተባባሪ ሃላፊ የሆኑት ሰርዳር አልታን፣ የጂን ኒውስ ኃላፊ ሳፊዬ አላጋስ እና የሜዞፖታሚያ የዜና ኤጀንሲ አዘጋጅ አዚዝ ኦሩክ ይገኙበታል።
ቱርክ ባለፋት አስርት አመታት በርካታ ጋዜጠኞችን ማሰሯ ተገልጿል
የቱርክ መንግስት ከኩርድ አማጺያን ጋር በተለያየ ጊዜ ጦርነት ውስጥ መግባቱ ይታወሳል፡፡ የኩርድ አማጺያን ወይም ፒኬኬ የታጠቀ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድርጅት ሲሆን ኩርዶች በሚበዙበት በደቡባዊ ቱርክ እና በሰሜናዊ ኢራቅ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡