ሚሳዔሉን ከተዋጊ ጄቶች፣ ድሮኖች፣ ከጦር ተሸከርካሪዎችና ከመርከቦች ላይ ማስወንጨፍ ይቻላል
የቱርኩ የመከላከያ መሳሪያ ትጥቅ ማምረቻ ተቋም ሮክስታን “ቻኪር” የተባለ አዲስ ክሩዝ ሚሳዔል ሰርቶ ይፋ አድርጓል።
አዲሱ ክሩዝ ሚሳዔል “ቻኪር” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፤ ከየብስ፣ ከአየር፣ ከባህር እና ከተሸከርካሪ ላይ የሚወነጨፍ መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ተነግሯል።
“ቻኪር” ሚሳዔል በ150 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ የሚገኝ የጠላትን ኢላማ ያለምንም ችግር መምታት እንደሚችልም ነው የመከላከያ ተቋው ሮክስታን ያስታወቀው።
በሚሳዔሉ ላይ በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ሙከራ ይደረግበታል ይባለ ሲሆን፤ በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2023 አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ነው የተገለፀው።
በ150 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ የሚገኝ የጠላትን ኢላማ ይመታል የተባለው ሚሳዔሉ፤ ከጦር ተሸከርካሪዎች፣ ከተዋጊ ጄቶች፣ ድሮኖች እና ከባህር ኃይል መርከቦች ላይ ማስወንጨፍ የሚቻል ነው ተብሏል።
ሚሳዔሉ ከመሬት እና ከባህር ላይ ኢላማዎች በተጨማሪ በዋሻዎች ውስጥ ያሉ የጠላት ኢላመዎችን ያለምንም ችግር መምታት የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
ልዩ ነው የተባለለት የጦር መሳሪያው በማንኛውም የአየር ፀባይ ውስጥ ኢላማዎችን መምታት የሚችል እና ከፍተኛ የሆነ ውድመት የሚያስከትል መሆኑንም የመከላከያ ተቋው ሮክስታን አስታውቋል።
ቻኪር ሚሳዔል ባለው ልዩ ዲዛይን አማካኝነት ከራዳር እይታ ውጪ መሆን የሚችል መሆኑን ነው የተገለፀው